Fana: At a Speed of Life!

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት እና የትራንስፖርት ሚኒስቴር በተጓተቱ የመንገድ መሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች ላይ የሚታዩ የአፈጻጸም ማነቆዎችን ለመፍታት ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 22 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት እና የትራንስፖርት ሚኒስቴር በተጓተቱ የመንገድ መሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች ላይ የሚታዩ የአፈጻጸም ማነቆዎችን ለመፍታት ተወያዩ፡፡

በትራንስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ካሳሁን ጎፌ አወያይነት የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የኢኮኖሚ እቅድ አፈጻጸም ክትትል ዘርፍ፣ የኮንስትራክሽን ስራዎች ተቆጣጣሪ ባለስልጣን፣ የአትዮጵያ ቴሌኮሙዩኒኬሽን ኮርፖሬሽን እና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በተገኙበት ነው ውይይቱ የተደረገው፡፡

በውይይቱም የተጓተቱ የመንገድ መሰረተ ልማት ፕሮጀክቶችን አፈጻጸም በመስክ ተገኝቶ በመገምገም አፈጻጸሙ የሚገኝበትን ደረጃ እና በአፈጻጸም ሂደት የታዩ ማነቆዎችን በመለየት ተካሂዷል፡፡

በውይይቱ ከአጋር አካላት ጋር ተናቦ አለመሄድ ለፕሮጀክቶቹ መጓተት በምክንያትነት ቀርቧል፡፡

በአፈጻጸም የደከሙትን 11 ፕሮጀክቶች ችግሮች በመፍታት በተያዘላቸው ጊዜ አጠናቆ ለአገልግሎት ለማብቃት ሁሉም ተቋማት የየራሳቸውን የተናጥል እቅድ በማውጣት፣ ለፕሮጀክቶቹ መጓተት ምክንያት የሆኑትን ተጠያቂ በማድረግ ሊሰራ እንደሚገባ አቶ ካሳሁን አሳስበዋል።

በሌላ በኩል የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት የመስመር ማዛወር ስራዎችን በወቅቱ በማከናወን እና እንደ ሲሚንቶና ሌሎች አስፈላጊ ግብዓቶችን ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር ተወያይቶ በመፍታት መጓተት የታየባቸውን 11 ፕሮጀክቶች በቀጣይ 3 ወራት እንዲጠናቀቁ እና ለአገልግሎት እንዲበቁ በቅንጅት መሠራት እንዳለበት ከትራንስፖርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.