የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያን ለማዳን እንዘምታለን፤ ኢትዮጵያን ለማልበስ እንተክላለን- ጠ/ሚ ዐቢይ

By Melaku Gedif

July 30, 2021

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 23፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ኢትዮጵያ አሁን የገጠማትን ፈተና በድል ትሻገረዋለች አሉ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትዊተር ገፃቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ፥ ኢትዮጵያ አሁን የገጠማትን ፈተና በድል ትሻገረዋለች ብለዋል፡፡

“በድል የምትሻገረውን ኢትዮጵያ ለማልበስ አረንጓዴ አሻራችንን እናሳርፍ” ሲሉም መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

“ለዚህም ኢትዮጵያን ለማዳን እንዘምታለን፤ ኢትዮጵያን ለማልበስ እንተክላለን” ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!