ስፓርት

የከተማ አስተዳደሩ ለኢትዮጵያ ቡና እና ቅዱስ ጊዮርጊስ የስታዲየም መገንቢያ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ሰጠ

By Tibebu Kebede

January 28, 2020

አዲስ አበባ፣ ጥር 19፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለኢትዮጵያ ቡና እና ቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለቦች የስታዲየም መገንቢያ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ሰጠ።

የስታዲየም እና የስፖርት ማዕከል መገንቢያ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታውን ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ለኢትዮጵያ ቡና እና ቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለቦች ማስረከባቸውን የከተማ አስተዳደሩ ፕሬስ ሰክሬታሪ መረጃ ያመለክታል።