
ከእንጉዳይ የሚሰራው መድሃኒት የካንሰር ህመምተኞችን ድብርትና ጭንቀትን ይቀንሳል ተባለ-ጥናት
አዲስ አበባ፣ ጥር 19፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ከእንጉዳይ የሚሰራ መድሃኒት “psilocybin” የካንሰር ህመምተኞችን ድብርትና ጭንቀት እንደሚቀንስ ጥናት አመለከተ።
በካንሰር በሽታ ከተያዙ ሰዎች መካከል አንድ ሦስተኛ የሚሆኑት በጭንቀት፣ በድብርት እና ለሌሎች ስሜት መረበሾች እንደሚጋለጡ በጥናቱ ተመልክቷል።
በእንጉዳዮች ውስጥ ከሚገኝ “ፒሲሎሲቢን/psilocybin” ከተባለ ንጥረ ነገር የተሰራ መድሃኒት በካንሰር ህመምተኞች ላይ ከሚከሰት ድብርት እና ጭንቀት ስሜት ለረጅም ጊዜ እፎይታን እንደሚሠጥ በጥናቱ ተገልጿል።
ከፒሲሎሲቢን የተወሰነ መጠኑን ከስነ-ልቦና ሕክምና ጋር የወሰዱ ህመምተኞች ከ4 ዓመት በላይ የጭንቀት ፣ የድብርት ፣ የተስፋ መቁረጥ እና የሞት ጭንቀት መቀነሳቸው ነው የተነገረው።
በኒው ኤንዋይ የአእምሮ ሳይንስ ዲፓርትመንት የአእምሮ ሳይንስ ፕሮፌሰር እስጢፋኖስ ሮስ፥ ይህ ግኝት ፒሲሎሲቢን ቴራፒ ለሕይወት አስጊ በሆነ ካንሰር የተያዙ ህመምተኞችን ስሜት፣ ሥነ ልቦናዊ እና መንፈሳዊ ደህንነትን ለማሻሻል ተስፋ ሰጪ ዘዴ ነው ብለዋል።
ጥናቱ መነሻ ያደረገው በፈረንጆቹ በ2016 ቡድኑ ለመጀመሪያ ጊዜ ሪፖርት ባደረገው ማሻሻያ ላይ የተመሰረተ ነው ተብሏል።
በዚህም ለ29 ህመምተኞች ከካንሰር ህመም ጋር ተያይዞ ለተከሰተባቸው ጭንቀትና ድብርት በመጀመሪያ ደረጃ አንድ ፒሲሎሲቢን ወይም ፕላሴፖ ኒሲን ተብሎ በሚጠራ ቫይታሚን እንዲወስዱ የተደረገ ሲሆን÷ ከ7 ሳምንታት በኋላ ተቃራኒው ከ9 የስነ ልቦና ሕክምናዎች ጋር ተጣምሮ እንደተሰጣቸው ጥናቱ ተቁሟል።
በዚህም ሁሉም ህመምተኞች መድሀኒቱን ከወሰዱ በኋላ በ6 ወራት ጊዜ ውስጥ ከ60 እስከ 80 በመቶ የሚሆኑት በከባድ ድብርት፣ በጭንቀት እና በጭንቀት እና በሞት ላይ የተሻሻሉ አመለካከቶችን ማሳየታቸው ታውቋል።
ከ15ቱ የመጀመሪያዎቹ ተሳታፊዎች ከ3 ነጥብ 2 እና ከ 4 ነጥብ 5 ዓመታት በኋላ ተከታትለው የቆዩና ዘላቂ የረጅም ጊዜ ማሻሻያዎችን ያሳዩ ሲሆን፥ ከእነዚህ ውስጥ ከ70 በመቶ በላይ የሚሆኑት በህይወት ልምዳቸው ላይ አዎንታዊ ለውጥ ማምጣት የቻሉ መሆናቸው በጥናቱ ተመላክቷል።
የጥናት ቡድኑ መድሀኒቱ ሙሉ በሙሉ እንዴት አዕምሮ ላይ ተጽእኖ መፍጠር እንደሚችል ባይገልጹም፤ አንጎል የነርቭ ሴል ደረጃ ስላለው ከተለያዩ ልምዶች ጋር የመላመድና የመቀየር ችሎታ ስላለው መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በካንሰር በሽተኞች መካከል ጭንቀትንና ድብርት ለማከም አማራጭ መንገድ በአፋጣኝ ያስፈልጋልም ነው የተባለው።
በቅርብ በተደረገው ጥናት አነስተኛ ቁጥር ያላቸው ህመምተኞች ላይ ቁጥጥር መደረጉ እና ከቀዳሚው ሙከራ ጋር መደራረብ ያሉባቸው በመሆኑ የጥናቱ ውስንነቶች ናቸው ተብሏል’
በፈረንጆቹ በ2018 በዓለም ዙሪያ ወደ 18 ሚሊየን የሚጠጉ የካንሰር በሽታ ተጠቂዎች እንደነበሩ የዓለም ጤና ድርጅት ጥናቶች ያመለክታሉ።
ምንጭ፦ ሲ.ኤን.ኤን