Fana: At a Speed of Life!

በህዳሴ ግድብ የታየውን አንድነት ህወሓትን ለማስወገድ መጠቀም ይገባል ኢ/ር ከማል ሙሃመድ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 23፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ዜጎች በህዳሴ ግድብ ግንባታና የውሃ ሙሌት ያሳዩትን አንድነት አሸባሪውን ህወሓት ለማስወገድም ሊጠቀሙበት እንደሚገባ የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ዶክተር ኢንጂነር ከማል ሙሃመድ ገለጹ፡፡
ኢንጂነር ከማል በኮምበልቻ ከተማ የዘመቻ ህልውና የክተት አዋጅ የንቅናቄ መድረክ ላይ÷”በአሁኑ ወቅት የገጠመን ፈተና ከፍተኛ መስዋዕትነት የሚያስከፍለን ቢሆንም ቅኝ ገዢዎችንና ባንዳወችን አሳፍሮ መመለስ የኢትዮጵያውያን የጀግንነት ባህሪ ነው” ብለዋል፡፡
“ኢትዮጵያ በምታደርገው የብልጽግና ጉዞ ምቾት ያልተሠማቸው የውጭ ሃይሎችና ሀገር የካዱ የውስጥ ጠላቶቻችን ልዩነታችንን አግንነው እርስ በርሳችን አጋጭተው ኢትዮጵያን ለማፍረስ እየሰሩ ነው” አስረድተዋል፡፡
ኢትዮጵያውያን በህዳሴ ግድብ ግንባታና የውሃ ሙሌት ያሣዩትን አንድነት አሁንም ሀገርን ለመበተን እየሠራ ያለውን የ አሸባሪውን የትህነግ ቡድንንና አስተሣሠቡን በማስወገድ ሊጠቀሙበት ይገባልም ነው ያሉት፡፡
በፕሮግራሙ ላይ የተሳተፉት የሃይማኖት አባቶችም ለሀገር መሞትና ከህዝብ ፊት መቆም ሰማዕትነት እንጅ ሞት አይደለም ብለዋል፡፡
ዘመናዊ ቅኝ ተገዥ ሊያደርጉ ለተነሱ ሁሉ እንኳን ልጆቻችን እኛም እንደ አባታችን አቡነ ጴጥሮስ ለመሥዋዕትነት ዝግጁ ነን ነው ያሉት፡፡
የኮምቦልቻ ከተማ ወጣቶችም ከመንደር እስከ ግንባር ሀገራችንን ለመጠበቅ ጠሪ አያሻንም ላለፋት 27 ዓመታት ያሣለፍነው ጊዜ ይበቃናል ብለዋል፡፡
በአለባቸው አባተ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.