Fana: At a Speed of Life!

12ኛው ሁሉን አቀፍ የአፍሪካ የቆዳና የቆዳ ውጤቶች አውደ ርዕይ በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 23፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) 12ኛው ሁሉን አቀፍ የአፍሪካ የቆዳና የቆዳ ውጤቶች አውደ ርዕይ በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው፡፡
አውደ ርዕዩ እንደ አውሮፓውኑ አቆጣጠር ከመጪው ህዳር 3- 6 ባሉት ቀናት ነው በአዲስ አበባ ከተማ የሚካሄደው፡፡
በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነው የቆዳና የቆዳ ውጤቶች ቴክኖሎጂ አውደ ርዕይ በተባበሩት መንግስታት የልማት ግብ እና በአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጠና ላይ ትኩረቱን እንደሚያደርግ ይጠበቃል፡፡
በአውደ ርዕዩ የምስራቅ አፍሪካ የቆዳ አምራቾች ለአለም አቀፉ ፋሽን ብራንድ እና ገዢዎች የተመረጡ ስራዎቻቸውን እና ምርቶቻቸውን እንደሚያቀርቡ ከንግድ እና ኢንደስትሪ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.