Fana: At a Speed of Life!

ኒውዚላንድ ለኢትዮጵያ ምርጫ ማስፈፀሚያ የሚውል የ1 ነጥብ 6 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ አደረገች

አዲስ አበባ፣ ጥር 19፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኒውዚላንድ ለቀጣዩ የኢትዮጵያ ምርጫ ማስፈፀሚያ የሚውል የ1 ነጥብ 6 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ድጋፍ አደረገች።

የድጋፍ ስምምነቱንም በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የልማት ፕሮግራም የኢትዮጵያ ተወካትይ ቱርሃን ሳለህ በኢትዮጵያ የኒውዚላንድ አምባሳደር ማርክ ራምስደን ጋር ተፈራርመዋል።

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የልማት ፕሮግራም የኢትዮጵያ ተወካይ ቱርሃን ሳለህ በትዊተር ገፃቸው ባስተላለፉት መልእክተም፥ የኒውዚላንድ መንግስት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ታማኝ የሆነ ምርጫ እንዲያካሂድ የሚደግፈውን ጥምረት በመቀላቀሉ ምስጋና አቅርበዋል።

ከዚህ ቀደምም ለቀጣዩ የኢትዮጵያ ምርጫ ዴንማርክ የ1 ነጥብ 5 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር፣ ፊንላንድ የ800 ሺህ ዩሮ እንዲሁም ሌሎች ሀገራትም በተመድ የልማት ፕሮግራም በኩል ለቀጣዩ የኢትዮጵያ ምርጫ ድጋፍ ማድረጋቸው ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የቀጣዩ ሃገራዊ ምርጫ ረቂቅ የጊዜ ሰሌዳ ይፋ ማድረጉ የሚታወስ ሲሆን፥ ነሃሴ 10 ቀን 2012 ዓ.ም የድምጽ መስጫ ቀን እንዲሆን ረቂቅ የጊዜ ሰሌዳው ተቀምጧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.