የሀገር ውስጥ ዜና

በሱዳን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በአሸባሪው ህወሓት ላይ የሚወሰደውን እርምጃ በመደገፍ ሰልፍ አደረጉ

By Tibebu Kebede

July 31, 2021

አዲስ አበባ ፣ሐምሌ 24፣ 2013 ( ኤፍ ቢ ሲ) በሱዳን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በአሸባሪው ህወሓት ላይ የሚወሰደውን እርምጃ በሚችሉት ሁሉ እንደግፋለን ሲሉ ድምጻቸው በአደባባይ አሰምተዋል።

ሰልፈኞቹ በካርቱም ባሰሙት ድምጽ፥ በኢትዮጵያ መንግስት ላይ የውጭ ጫናንና ጣልቃ ገብነትን አጥብቀው አውግዘዋል።

በሱዳን የኢትዮጵያ ኢምባሲ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ ሰልፈኞቹ የአገራቸው ጉዳይ አሳስቧቸው ለመንግስት ድጋፍ ለመስጠትና ጫናዎችን ለማውገዝ ወደ አደባባይ መውጣታቸውን አመስግነዋል ።

ሽብርተኛው ቡድን ህጻናት ፣ሴቶችን እና አረጋዊያንን በማሰለፍ እየፈጸመ ያለውን ትንኮሳ ሊወገዝ ይገባል ማለታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!