በአሻባሪው ሕወሓት የተገደሉ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር አባላት በሻማ ማብራት ታስበዋል
አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 24 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሻባሪው ሕወሓት የተገደሉ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር አባላትን የሚዘክር የሻማ ማብራት ሥነ-ስርዓት በመስቀል አደባባይ ተካሄደ፡፡
በአሻባሪው ሕወሓት በተለያዩ የትግራይ ከተሞች የተገደሉ ከ100 በላይ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር አባላትን የሚዘክር የሻማ ማብራት ሥነ-ስርዓት በመስቀል አደባባይ ተካሄዷል።
አሸባሪው ህወሓት የሀገር መከላከያ ሰራዊት ከትግራይ ከወጣ በኋላ ከጊዜያዊ አስተዳደሩ ጋር ሰርታችኋል፤ ተባብራችኋል በሚል በሀገረ ሰላም የተገደለችውን ነፍሰጡር አመራር ጨምሮ ከ100 በላይ ሰዎችን በአደባባይ በግፍ ገድሏል።
በዚህ የሻማ ማብራት ስነ ስርአት ላይ ዶክተር አብረሃም በላይን ጨምሮ፣ የጊዜያዊ አስተዳድሩ ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ሚሊዮን ኣብርሃ፣ የትዴፖ ሊቀመንበር ዶክተር አረጋዊ በርኸ ፣ የጊዜያዊ አስተዳደሩ አመራሮች፣ የተለያዩ ፓርቲ አመራሮች እና የትገራይ ተወላጆች መገኘታቸውን ኢፕድ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!