Fana: At a Speed of Life!

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ለአርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን የክብር ዶክትሬት ሰጠ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 24 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ለአርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) የክብር ዶክትሬት ሰጠ፡፡
 
ዩኒቨርሲቲው ዛሬ በይፋ በተከናወነ ስነ ስርአት ለአርቲስት ቴዎድሮስ የክብር ዶክትሬት ሰጥቷል፡፡
 
አርቲስቱ በክብር ዶክትሬት አሰጣጥ ስነ ስነ ስርዓቱ ላይ ባደረገው ንግግር÷ ሀገራችን ኢትዮጵያ አሁን ላይ ከመቼውም ጊዜ በላይ የገባችበት ከባድ አጣብቂኝና እጅግ ፈታኝ ሁኔታ በሁሉም ዘንድ የታወቀ መሆኑን አንስተዋል፡፡
 
እናት ከአስቸጋሪው ምጥ በኋላ ልጇን አይታ እንደምትደሰተው ሁሉ ሀገራችንም ከገጠማትና ሊገጥማት ከሚችለው ማንኛውም ከባድ አደጋ በድል ወጣ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት አሸናፊ እንደሚሆን ምንም ጥርጥር የለውም ነው ያለው፡፡
ላለፉት ቀላል ለማይባሉ ዓመታት ሀገራችንን አስጨንቆ የያዛት የጎሳ ፖለቲካ ሃሳብ እንደማንኛውም ፍልስፍናና ሃሳብ ተወልዶ አድጎ አርጅቶና በስብሶ ተፈጥሯዊ ሞቱን ሞቷል ሲልም ተናግሯል፡፡
 
ስለዚህ ከዚህ በኋላ መላው የኀገራችን ሀዝብ በተለይም ወጣቱ በጎሳና በዘር እንዲሁም በሃይማኖት ልዩነቶች ሳትናወጡ ከመቸውም ጊዜ በላይ በአንድነትና በፍጹም ኢትዮጵያዊ ብሄራዊ ስሜት በተጠንቀቅ ጸንታችሁ ወይም ጸንተን መኖር ያለብን መሆኑን ማሳስብ እወዳለሁ ብሏል፡፡

 

 

አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን ስለሀገር ፍቅር፣ ስለ ሰላም፣ ስለ አንድነት እንዲሁም ለበርካታ መሪዎች፣ አትሌቶች እና ጀግኖች በሙዚቃው አቀንቅኗል፡፡
 
የበጎ ስራዎችን ከመስራቱም ባለፈ በርካታ ሽልማቶችን ተቀብሏል፡፡
 
የጎንደር ከተማ አስተዳደርም በአርቲስት ቴዲ አፍሮ ስም ጎዳና እንዲሰየም ወስኗል፡፡
 
በሰላም አስመላሽ
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.