Fana: At a Speed of Life!

በሶማሌ ክልል በአንድ ጀንበር 2 ነጥብ 5 ሚሊየን ችግኞችን የመትከል መርሃ ግብር ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 24 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሌ ክልል በአንድ ጀንበር 2 ነጥብ 5 ሚሊየን ችግኞችን የመትከል መርሃ ግብር በዛሬው ዕለት በጅግጅጋ ከተማ ተካሂዷል።
በመርሃ ግብሩ የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሳሚ ረዲ፣ የሶማሌ ክልል የእርሻና ተፈጥሮ ኃብት ልማት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር አብዲቃድር ኢማን እና የተለያዩ የክልሉ ቢሮ ሃላፊዎች እንዲሁም የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን፣ የፌዴራል ፖሊስ አመራሮችና የወጣቶች ሊግ አባላት ተሳትፈዋል።
የግብርና ሚኒስትር ድኤታ አቶ ሳሚ ረዲ ÷ለጎረቤት ሀገራት ያለንን ችግኞች በማካፈል በጋራ ለማልማትና የአየር ንብረት ለውጥን በጋራ ለመከላከል የሚያስችል ስራ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
የሶማሌ ክልል እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ ሃላፊ ዶክተር አብዲቃድር ኢማን በበኩላቸው ÷ በየዓመቱ ሃምሌ 24 በመላው የክልሉ ዞኖች እና ከተማ አስተዳደሮች የሚካሄድው የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በዛሬው ዕለት መካሄዱን ገልፀዋል።
ሃላፊው ለአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ በቂ ዝግጅት መካሄዱን ጠቁመው÷ በክልሉ በሚካሄደው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ህብረተሰቡም የበኩሉን ተሳትፎ እንዲያደርግ ጥሪ አስተላልፈዋል።
በጅግጅጋ ከተማ የሚገኘው የፌዴራል ፖሊስ የምስራቅ ዲስትሪክት ሪጅን ፅህፈት ቤት ኮማንደር እሸቱ መሸሻ÷ ሠራዊቱ ህግን ከማስከበር ስራ ጎን ለጎን ከ500 በላይ ችግኞች በመትከል በሀገራገሪቱ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ተሳትፎ ማድረጋቸውን ገልፀዋል።
በክልሉ በዘንድሮው 3ኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በክልሉ በአጠቃላይ ከ2 ነጥብ 5 ሚሊየን ችግኞችን የመትከል ዕቅድ ተይዞ ነው ተግባራዊ እየተደረገ የሚገኘው።
ከተያዘው እቅድ ውሰጥ እስከ አሁን ባለው አፈፃፀም አራት ሚሊየን ችግኞችን በመትከል የእቅዱን 65 በመቶ ማከናወን መቻሉን የሶማሌ ብዙሃን መገናኛ ኤጀንሲ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.