ስፓርት

መቅደስ አበበ እና ዘርፌ ወንድማገኝ በሴቶች የ3000 ሜትር መሰናክል ማጣሪያ ውድድር ለፍፃሜ አለፉ

By Meseret Awoke

August 01, 2021

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 25፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)መቅደስ አበበ እና ዘርፌ ወንድማገኝ በሴቶች የ3000 ሜትር መሰናክል ማጣሪያ ውድድር ለፍፃሜ አልፈዋል።

እየተካሄደ በሚገኘው የቶኪዮ ኦሎምፒክ 2020 የ3000 የሴቶች መሰናክል ውድድር በተለያየ ምደብ ተደልድለው ውድድራቸውን ካደረጉት ሶስት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች መካከል ሁለቱ ማጣሪያውን ማለፍ ችለዋል።

መቅደስ አበበ በ9፡23.95 3ኛ ወጥታ ስታልፍ፥ ዘርፌ ወንድማገኝ በ9:20.01 4ኛ ወጥታ ያለፈች ሲሆን፥ ሎሚ ሙለታ በ9:45.81 10ኛ ወጥታ ማጣሪያውን አላለፈችም።

ማጣሪያውን ያለፋት ሁለቱ አትሌቶችም የፊታችን ረቡዕ በሚካሄደው የፍፃሜ ውድድር ላይ ኢትዮጵያን ወክለው እንደሚወዳደሩ ከአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!