Fana: At a Speed of Life!

ከ5ሚሊየን በላይ የቡና ችግኞች ለአርሶ አደሮች ተከፋፈሉ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 25፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)ቀርጫንሼ ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ከ5ሚሊየን በላይ የሚሆኑ የቡና ችግኞችን ለአርሶ አደሮች አከፋፍሏል፡፡
የቡና ችግኞቹ የተሻሻለ ዝርያ ያላቸውና የተሻለ ምርት ሊያስገኙ እንደሚችሉ የተገለጸ ሲሆን ÷ ችግኞቹ የተከፋፈሉትም በምዕራብ ጉጂ ዞን ኮቸሬ ወረዳ ለሚገኙ አርሶ አደሮች መሆኑ ታውቋል፡፡
የዞኑ አስተዳዳር ተወካይ አቶ ዘማች መኩሪያ ባለሀብቱ እያደረጉት በሚገኘው ድጋፍ አርሶ አደሮች ደስተኛ መሆናቸውንና ዞኑም በከፍተኛ ደረጃ ቡና አምራች ከመሆኑ አንጻር የተከፈፋፈሉት ችግኞች የቡና ልማቱን ለማፋጠን ያላቸው ፋይዳ የጎላ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
እንዲሁም ባለሀብቱ እያደረጉት ባለው ተግባር ሊመሰገኑ እንደሚገባና ለወደፊቱም ይህንኑ አጠናክረው ይቀጥሉ መጠየቃቸውን ከኢትዮጵያ ቡና እና ሻይ ባለስልጣን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ከፌዴራል ቡናና ሻይ ባለስልጣን ተወክለው የተገኙት አቶ ሳህለማርያም ገብረመድህን በበኩላቸው÷ መንግስት የቡናን ምርት እና ምርታማነት ለመጨመር፣ በግብይቱ ላይ የሚታዩ ችግሮችንም በዘለቄታው ለመፍታት የሚስችሉ በርካታ ስራዎች በመሰራት ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.