የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የልዩ ሀይል ፖሊስ ደምብ ልብስ ሊቀይር ነው
አዲስ አበባ ፣ሐምሌ 26፣ 2013 ( ኤፍ ቢ ሲ)የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የልዩ ሀይል ፖሊስ ደምብ ልብስ ሊቀይር መሆኑ ተገለጸ፡፡
ኮሚሽኑ ደምብ ልበሱን ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚያደርግ የክልሉ ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነርና የአድማ ብተናና የልዩ ሀይል አዛዥ ረዳት ኮሚሽነር እንዳለ አበራ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ገልጸዋል።
ደምብ ልብሱ ላለፉት አስር አመታት ያገለገለ በመሆኑ የመቀየሩ ምክንያት አንዱ ሲሆን፥ ደምብ ልብሱ በተለያዩ ምክንያት ከልዩ ሀይል አባልነት ከሚወጡና ከሚሸኙ ፖሊስ መኮንኖች ብዙ ሰዉ እጅ እንደገባ ይታመናል ብለዋል ረዳት ኮሚሽነሩ።
ይህ ደግሞ የአድማ ብተናና ልዩ ሀይል አባልን በመምሰል የተለያዩ የህገወጥ ተግባራት ሊከናወንበት እንደሚችልና ከዚህ በፊትም ያጋጠመ ተግባር መሆኑን ገልጸዋል።
መሰል ድርጊቶች የልዩ ሀይሉን የተመሰገነ ስም ለማጠልሸት ለሚፈልጉ አካላት አመቺ ሁኔታን የሚፈጥር በመሆኑ ይህን ለመከላከል የሚያግዝ መሆኑን አስረድተዋል።
ደምብ ልብሱ በጥራት ተሰርቶ ለአባላቱ ይዳረሳልም ተብሏል።
በጌታቸዉ ሙለታ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!