Fana: At a Speed of Life!

የተሻለ የስራ አፈፃፀም ላስመዘገቡ የፌዴራል ፖሊስ አመራሮችና አባላት እውቅና ተሰጠ

አዲስ አበባ ፣ሐምሌ 26፣ 2013 ( ኤፍ ቢ ሲ)የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ዘርፍ ዲፕሎማቲክ ጥበቃ ዲቪዥን የተሻለ የስራ አፈፃፀም ላስመዘገቡ አመራሮችና አባላት እውቅና ተሰጥቷል፡፡
የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ዘርፍ በአዲስ አበባ የሚገኙ ፀረ ሸብርና የተደራጁ ወንጀለኞች ዳይሬክቶሬት ዲፕሎማቲክ ጥበቃ ዲቪዥን፣ማስተባበሪያ 1፣ ኃይል 3 በ2013 በጀት ዓመት የተሻለ የስራ አፈፃፀም ላስመዘገቡ አመራሮችና አባላት የእዉቅናና የሽልማት የመስጠት ፕሮግራም አካሂዷል፡፡
የፀረ ሸብርና የተደራጁ ወንጀለኞች ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮማንደር በላይ ከበደ እንደገለጹት፥ በምንጠብቃቸዉ ሀገር ዓቀፍና አለም ዓቀፍ ተቋማትና ኤምባሲዎች ላይ የፀጥታ ችግር እንዳይደርስ ውጤታማ የሆኑ ስራዎችን ሰርተናል ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ ጠላቶቿን በማሸነፍ ታፈርሳለች እንጂ አትፈርስም ያሉት ዳይሬክተሩ፥ አሸባሪው የጁንታ ቡድን በሀገራችን ህልውና ላይ የተቃጣውን አደጋ በቁርጠኝነት በመመከት በአሁኑ ጊዜ የገጠመንን የፀጥታ ችግር እናልፋለን ሲሉ ተናግረዋል፡፡
አሸባሪውን የህወሓት ጁንታ ቡድን በመደምሰስ የሚገኘዉ ድል እንደተጠበቀ ሆኖ ዝግጁነታችን የበለጠ በማጠናከርና ተግተን በመስራት ሀገር ዓቀፍና አለም ዓቀፍ ተቋማቱንና ኤምባሲዎቹን ከፀረ ስላም ኃይሎች መጠበቅ ይኖርብናል ሲሉም አሳስበዋል፡፡
በወንጀል መከላከል ዘርፍ ዲፕሎማቲክ ጥበቃ ዲቪዥን ምክትል አዛዥ ኮማንደር ሂካ ዋቅላታ በበኩላቸው፥ በአዲስ አበባ በተለያዩ አካባቢዎች የምንጠብቃችውን ተቋማትና ኤምባሲዎች ላይ ምንም አይነት አደጋ እንዳይደርስ በቁርጠኝነት እየሰራን ነው ብለዋል፡፡
የተሻለ የስራ አፈፃፀም ላስመዘገቡ አመራሮችና አባላት ሽልማትና ሴርተፍኬት መበርከታቸውን ከፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.