Fana: At a Speed of Life!

የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ቦርድ አባላትና አጋር አካላት የአውራምባ ማህበረሰብን ጎበኙ

አዲስ አበባ ፣ሐምሌ 26፣ 2013 ( ኤፍ ቢ ሲ) የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ቦርድ አባላትና አጋር አካላት የአውራምባ ማህበረሰብን ጎበኙ።
የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳዮች ሚኒስትር እንዲሁም የዩኒቨርሲቲው ቦርድ ሰብሳቢ ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ፣ የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር አነጋግረኝ ጋሻው እና የሂዩማን ብሪጅ አፍሪካ ዋና ዳይሬክተር የክብር ዶክተር አዳሙ አንለይ የአውራምባ ማህበረሰብን ጎብኝተዋል።
በጉብኝታቸውም ከአውራምባ ማህበረሰብ መስራችና መሪ የክብር ዶክተር ዙምራ ኑሩ ጋር ውይይት አድርገዋል።
በቀጣይ ማህበረሰቡን በተለያየ መንገድ ማገዝ በሚቻልባቸው አማራጮች ላይ መምከራቸውን ከደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.