ስፓርት

በቶኪዮ ኦሊምፒክ በወንዶች መሰናክል ለሜቻ ግርማ ለኢትዮጵያ የብር ሜዳሊያ አስገኘ

By Feven Bishaw

August 02, 2021

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 26፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በቶኪዮ ኦሊምፒክ ዛሬ 9፡15 በተካሄደው የወንዶች 3000 ሜትር መሰናክል ሩጫ ውድድር ለሜቻ ግርማ ለኢትዮጵያ የብር ሜዳሊያ አስገኝቷል፡፡

በዚህም ለሜቻ ግርማ  ለኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የብር ሜዳሊያ  ሲያስገኝ  ጌትነት ዋለ ውድድሩን በአራተኝት አጠናቋል፡፡

ሞሮኳዊው አትሌት ሶፊያን ኤል ባካሊ ውድድሩን ሲያሸንፍ ኬንያዊው አትሌት ኪገን ቤንጃሚን ሶስተኛ በመሆን አጠናቋል፡፡