Fana: At a Speed of Life!

የክተት ጥሪውን በመቀበል ወደግንባር ለማቅናት የወሰኑ ሰራተኞች ሸኝት ተደረገላቸው

አዲስ አበባ ፣ሐምሌ 26፣ 2013 ( ኤፍ ቢ ሲ)የሀገር አንድነትን አደጋ ላይ ለመጣል የሚሰራው ህገ-ወጥ ቡድን ላይ እየተወሰደ ያለውን እርምጃ በመደገፍ ለመዝመት የቆረጡ አራት የገቢዎች ሚኒስቴር ሰራተኞች በዛሬው ዕለት ሽኝት ተደረገላቸው፡፡

በሽኝት ፕሮግራሙ ላይ “ሀገር እንዳትፈርስ ውድ ህይወታችሁን ለመስጠት ስለወሰናችሁ እናመሰግናለን” ብለዋል የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው፡፡

አማፂው የህወሓት ጁንታ ቡድን ”እኔ የማልዘውራት ሀገር ትፍረስ” በሚል የማይሳካ ህልም እንዲመክን መላው ኢትዮጵያውያን የጀመሩትን ትግል ለመቀላቀል የወሰኑ ሰራተኞቻችን ትልቅ ክብር አለንም ነው ያሉት፡፡

የሚጠበቅብንን ሀገራዊ ሀላፊነት ተወጥተን ገቢ በአግባቡ መሰብስብ ማለት ጁንታውን እንደመደምሰስ ይቆጠራልም ነው ያሉት፡፡

በቀጣይም ሰራዊቱን በገንዘብ እና በቁሳቁስ ለመደገፍ የተጠናከረ ስራ እንደሚጠበቅ ገልፀው÷ ለዚህም መላው ሰራተኛ ቁርጠኛ መሆን እንዳለበት ጠቁመዋል፡፡

በሽኝት መርሀ ግብሩ ላይ የተገኙት ዘማች ሰራተኞች በበኩላቸው÷ የተጋረጠብንን ሀገራዊ አደጋ ለመመከት ሁሉም በአቅሙ መደገፍ አለበት ብለዋል፡፡

መላው የገቢዎች ሰራተኞችና እና አመራሮች የተጣለባቸውን ሀላፊነት ከየትኛውም ጊዜ በላይ እንዲወጡና ግንባር ላለው ሰራዊት ደጀን እንዲሆኑ ጠይቀዋል፡፡

ከዘማቾቹ መካከል ሁለቱ በምስራቅ አዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ፅ/ቤት እና ሁለቱ ደግሞ በኮምቦልቻ ቅ/ፅ/ቤት ስር የሚገኙ መሆናቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.