Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ክልል ምክር ቤት ጉባኤ ከ49 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት አጸደቀ

አዲስ አበባ ፣ሐምሌ 26፣ 2013 ( ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት ጉባኤ ለ2014 የስራ ዘመን ከ49 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት አጸደቀ።
 
በጀቱ ከመደበኛ የመሥሪያ ቤቶችና ማዘጋጃ ቤቶች የውስጥ ገቢ እንዲሁም ከፌዴራል ድጎማና እርዳታ የሚሸፈን መሆኑ ተመልክቷል።
 
የክልሉ የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ሀላፊ አቶ ተፈሪ አባቴ በጀቱ በዋናነት ድህነት ቀናሽ በሆኑ የልማት ተግባራት እንዲሁም ለደመወዝና አስተዳደራዊ ጉዳዮች እንዲውል የተመላከተ መሆኑን አብራርተዋል።
 
ትምህርት፣ ጤና፣ መንገድና የመልካም አስተዳደር ጉዳዮችም ትኩረት እንደተሰጣቸው አስረድተዋል።
 
“በጀቱ ሰላምና ደህንነት፣ አዳዲስ የሥራ ዕድል ፈጠራዎች፣ አምራች ኢንዱስትሪዎችና መሰል ተግባራትን በማጠናከር ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ ትኩረት የተደረገበት ነው” ብለዋል።
 
ከፈጣን ኢኮኖሚያዊ ልማት ባሻገር ፍትሐዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የማህበራዊ አገልግሎቶች ተደራሽነትና ጥራት ማሳደግም ሌላው የበጀቱ ትኩረት መሆኑን አመልክተዋል።
 
የምክር ቤት አባላት በጀቱ በአግባቡ ህዝብን ሊጠቅሙ በሚችሉ የመሠረተ ልማቶችና ሥራ ዕድል ፈጠራ ላይ ድልድል እንዲደረግ ማሳሰባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.