የሀገር ውስጥ ዜና

ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በኢትዮጵያ ከአውስትራሊያ ጊዜያዊ አምባሳደር ጋር ተወያዩ

By Tibebu Kebede

August 02, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በኢትዮጵያ ከአውስትራሊያ ጊዜያዊ አምባሳደር ጄኒ ዳን ረን ጋር ተወያዩ።

በውይይታቸውም ቀጣይ በከተማ ደረጃ በሚተገቡ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ ሰፋ መክረው መግባባት ላይ መድረሳቸውን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

በዚህም በከተሞች የሁለትዮሽ ጉድኝት፣ በአቅም ግንባታ እንዲሁም በንግድና ኢንቨስትመንት ስራዎች ዙሪያ በጋራ ለመስራት መስማማተቸውንም አስታውቀዋል።

የአውስትራሊያ ጊዜያዊ አምባሳደር ጄኒ ዳን ረን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና በአውስትራሊያ ባለሀብቶች ድጋፍ ሊገነባ የታሰበውን “የልጆች ተስፋ” የወላጅ አልባና ችግረኛ ህጻናት ማሳደጊያና መንከባከቢያ ማዕከልን ግንባታ እውን ለማድረግ እስካሁን ከ200 ሚሊየን ብር በላይ መዘጋጀቱን ገልጸዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!