Fana: At a Speed of Life!

ህዝቡ አሸባሪው ትህነግ የከፈተበትን ጦርነት ለመመከት የፈጠረው ህብረት ኢትዮጵያዊነትን የሚያጠነክር እድል ፈጥሯል -የጎንደር ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 27፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)ህዝቡ አሸባሪው ትህነግ የከፈተበትን ጦርነት ለመመከት የፈጠረው ህብረት ኢትዮጵያዊነትን የሚያጠነክር እድል መፍጠሩን የጎንደር ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ተሾመ አግማስ ገለጹ፡፡

አሸባሪው ትህነግ በብሄር፣ በሃይማኖት፣ በፖለቲካና በሌሎች ከፋፋይ አጀንዳዎቹ ከፋፍዬ በትኜዋለሁ ያለው ህዝብ የተከፈተበትን ጦርነት ለመመከት የፈጠረው ህብረት ኢትዮጵያዊነት ጠንክሮ የሚወጣበትን እድል መፍጠሩን ነው ምክትል ከንቲባው ያስታወቁት፡፡

ለህልውና ዘመቻው ከከተማው 132 ሚሊየን ብር ገደማ መሰብሰቡንም ማመልከታቸውን ኢፕድ ዘግቧል፡፡

አቶ ተሾመ እንደገለጹት÷ ህዝቡ አሸባሪው ትህነግ የከፈተበትን ጦርነት ለመመከት የፈጠረው ህብረት ኢትዮጵያዊነት ጠንክሮ የሚወጣበትን እድል ፈጥሯል፡፡

ከፋፍዬ በትኜዋለሁ ብሎ ያሰበው ህዝብ እንደአሸባሪው ዓላማ ሳይሆን የተከፈተበትን ጦርነት ለመመከት በአንድነት እንዲሰለፍ ምክንያት እንደሆነለት ጠቁመው÷ አሸባሪው ትህነግ ከፋፍዬ ጨርሻለው ብሎ ያሰበው ከፋፋይ አጀንዳው በተቃራኒው ሆኖበታል ብለዋል፡፡

ከሁሉም የኢትዮጵያ ክፍሎች የተነቃነቀው ህዝብ የጥፋት ቡድኑን ለመደምሰስ ያሳየው አንድነትና ህብረት ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

በቡድኑ የታወጀበትን ጦርነት በአንድነትና በህብረት በመዝመት ክንዱን እያሳረፈበት ይገኛል ያሉ ሲሆን÷ አሸባሪው ህዝቡን በጐጥና በዘር ከፋፍሎ ኢትዮጵያን ለመበተን ያሴረው መክኖ በቆሰቆሰው እሳት መላው ህዝብ ቡድኑን ለመደምሰስ በአንድነትና በህብረት እንዲነሳ ምክንያት መሆኑንም አመልክተዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.