ስፓርት

በቶኪዮ ኦሎምፒክ ዛሬ የሚጠበቁ የፍፃሜ እና የማጣሪያ ውድድሮች

By Meseret Awoke

August 03, 2021

አዲስ አበባ ፣ሐምሌ 27፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በቶኪዮ ኦሎምፒክ ዛሬ ከሰዓት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ይጠበቃሉ፡፡

ዛሬ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ በሚደረገው የ5000 ሜትር ወንዶች ማጣሪያ ውድድር እንዲሁም ከቀኑ 9፡25 ላይ በሚደረገው የ800 ሜትር ሴቶች ፍፃሜ ላይ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ይወዳደራሉ፡፡

በ800 ሜትር ኢትዮጵያን ወክላ ሃብታም አለሙ ትሮጣለች፡፡

በ5000ሜትር ወንዶች ማጣሪያ ጌትነት ዋለ፣ ንብረት መላክ እና ሚልኬሳ መንገሻ እንደሚሳተፉ ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!