Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ 13ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን እያካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 27፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ 13ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን እያካሄደ ነው፡፡
በጉባኤው ላይ የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል፣ የሐይማኖት አባቶች፣ የክልሎችና የከተማ መስተዳድሮች የሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ ተወካዮች ተገኝተዋል።
ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል የኢትዮጵያ የሐይማኖት ጉባኤ ምዕመናን ችግር ሲገጥማቸው ከችግር የሚወጡበትን መንፈሳዊ ጥንካሬን ሲሰጥ መቆየቱን አንስተዋል፡፡
ይህም ኢትዮጵያ እንደ ሀገር እንድትቀጥል ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረጉንና ባለፉት ሦስት ዓመታት የገጠሙንን ችግሮች ጸሎትንና የመንፈስ ምግብን እንደ ስንቅ በመያዝ አብረን ተጉዘናል ነው ያሉት።
ሐይማኖትና መንግሥት በጋራ በመደጋገፍ ሥራዎችን እንደሚሰሩና ጉባኤውም ይህንን አቅጣጫ እንደሚያስቀምጥ እምነታቸው መሆነን አመልክተዋል።
ያለንበት ወቅት የሰላምና የብልጽግና ጉዞ ለማስቀጠል የምንሰራበት በሌላ በኩል ለዘመናት የተከማቹ ችግሮች የተከሰቱበት በመሆኑ ችግሮቹን በመቅረፍ የትስስር ሰንሰለት የምንቀጥልበትን መንገድ ለመስራት የሐይማኖት አባቶች ሚና ከፍተኛ ነው ብለዋል።
ይህንንም ለማድረግ የሐይማኖት አባቶች ሚና ሰፊ ድርሻ ያለው በመሆኑ ፈተናውን በጋራ ጸንቶ ማለፍ ለድርድር የሚቀርብ ጉዳይ አደለም ሲሉም ተናግረዋል።
በጸሎት በምሕላ ኢትዮጵያ ጸንታ የምትቆምበትን መንገድ እንድትሰሩ ያስፈልጋል በማለት አመልክተዋል።
የኢትዮጵያ ሐይማኖት ተቋማት ጉበኤ የሥራ አስፈጻሚ ቦርድ ሰብሳቢ ብጹዕ አቡነ ጎርጎርዮስ በበኩላቸው የሐይማኖት አባቶች እውነተኛ የሰላም ሐዋርያ በመሆን ልንሰራ ይገባናል ብለዋል።
የአገር ሰላም በምኞትና ፍላጎት ብቻ አይመጣም፣ ጽኑ ተከታታይና ሰፊ ስራ በመሥራት የሚገኝ ውጤት መሆኑን ልንገነዘብ ይገባናል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.