ስፓርት

በ5000 ሜትር ወንዶች አትሌት ሚልኬሳ መንገሻ ለፍፃሜ አለፈ

By Meseret Awoke

August 03, 2021

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 27፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)በ5000 ሜትር ወንዶች አትሌት ሚልኬሳ መንገሻ ለፍፃሜ አልፏል፡፡

እየተካሄደ ባለው የቶኪዮ ኦሎምፒክ በሁለት ምድብ ተካፍሎ በተካሄደው የ5000 ሜትር ወንዶች ማጣሪያ ውድድር ላይ ከተካፈሉት አትሌቶች መካከል አትሌት ሚልኬሳ መንገሻ ሲያልፍ÷ አትሌት ጌትነት ዋለ እና አትሌት ንብረት መላክ ሳያልፉ ቀርተዋል፡፡

አትሌት ሚልኬሳ መንገሻ በ13፡31.13 በሆነ ሰዓት 6ኛ በመውጣት ፍፃሜውን ተቀላቅሏል፡፡

አትሌት ጌትነት ዋለ በ13፡41.13 9ኛ ደረጃ እንዲሁም አትሌት ንብረት መላክ በ13፡45.81 በሆነ ሰዓት 14ኛ ደረጃ ይዘው አጠናቀዋል፡፡

የፍፃሜ ውድድሩ የፊታችን አርብ ከቀኑ 9፡00 ሰዓት እንደሚካሄድ ከአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!