Fana: At a Speed of Life!

በሶማሌ ክልል ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ሲያዘዋውሩ የነበሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ፣ ጥር 20፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሶማሌ ክልል ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ሲያዘዋውሩ የነበሩ ተጠርጣሪዎች በትናንትናው ዕለት በቁጥጥር ስር ዋሉ።

የሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል ከጅግጅጋ ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው መጋሎቀረን መቆጣጠሪያ ጣቢያ ባደረገው ድንገተኛ ፍተሻ በቶጎጫሌ ድንበር በህገወጥ መንገድ በአንድ ተሽከርካሪ ተደብቆ ሊገባ የነበረ 39 ሽጉጥ ከተጠርጣሪዎቹ ጋር መያዙ ተጠቁሟል።

በዚህም ህገ ወጥ መሳሪያውን ይዘው የነበሩት ሶስት ተጠርጣሪዎች እና አንድ ተሽከርካሪ መያዙን የክልሉን ልዩ ኃይል ጠቅሶ የሶማሌ ክልል ሬዲዮና ቴሌቪዥን ዘግቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.