Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አባላት በከተማዋ በግንባታ ላይ የሚገኙ ሜጋ ፕሮጄክቶችን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 27፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አባላት በከተማዋ በግንባታ ላይ የሚገኙ ሜጋ ፕሮጄክቶችን ጎበኙ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ዘርፈሽዋል ንጉሴ÷ የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴዎች እና አባላት በጋራ በመሆን የአድዋ ዜሮ ዜሮ ፕሮጄክት ያለበትን ሁኔታ ጎብኝተዋል።
አፈ ጉባኤዋ በከተማዋ እየተገነቡ የሚገኙት ሜጋ ፕሮጀክቶች ታሪክን በሚዘክር መልኩ በተቀመጠላቸው ጊዜ ግንባታቸው እየተከናወነ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ በአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጠት የሚያስችሉ የተለያዩ ሜጋ ፕሮጄክቶች እና የቢሮ ህንፃ ግንባታዎች እየተከናወኑ መሆኑን የገለፁት አፈ ጉባኤዋ÷ ሁሉም ግንባታዎች በተያዘላቸው ጊዜ እና ጥራት እንዲጠናቀቁ ምክር ቤታቸው የክትትልና ቁጥጥር ስራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡
ለምክር ቤቱ አባላት ስለፕሮጀክቶቹ ማብራሪያ የሰጡት ታላላቅ ሜጋ ፕሮጀክቶች ጽህፈት ቤት ምክትል ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር መሬሳ ልክሳ÷ ለአድዋ ዜሮ ዜሮ ፕሮጀክት ህንፃ ግንባታ 4 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር ተበጅቶለት እየተከናወነ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
ፕሮጄክቱ በሚቀጥሉት ጥቂት ወራት ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት ይሆኖል ማለታቸውን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.