የሀገር ውስጥ ዜና

157 ሰብዓዊ ዕርዳታ የያዙ የጭነት መኪናዎች መቀሌ ደረሱ

By Meseret Awoke

August 04, 2021

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 28፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በትናንትናው ዕለት 157 ሰብዓዊ ዕርዳታ የያዙ የጭነት መኪናዎች መቀሌ መድረሳቸውን ከወቅታዊ ሁኔታ መረጃ ማጣሪያ ገለጸ።

የምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ አስፈላጊ መገልገያዎችን የያዙት የጭነት መኪናዎች፣ ከዓለም የምግብ ድርጅት፣ እንደ ዩኒሴፍና ዩ.ኤን .ኤፍ.ፒ.ኤ ካሉ የተባበሩት መንግስታት ድርጅቶች፣ እንዲሁም ምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆነ ድጋፍን ለማቅረብ ከሚንቀሳቀሱ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የተገኘ ድጋፍን አካትተዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!