የሀገር ውስጥ ዜና

ከየመን፣ ሰንዓ 79 ዜጎች ወደ አገራቸው ተመለሱ

By Meseret Awoke

August 04, 2021

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 28፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ከየመን፣ ሰንዓ 79 ዜጎች ወደ አገራቸው ተመልሰዋል፡፡

በየመን የሚገኙ ዜጎች ወደ አገራችው ለመመለስ እየተደረገ ባለው ጥረት በትናንትናው ዕለት 79 ዜጎቻችን ከየመን፣ ሰንዓ ወደ አገራቸው መመለሳቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ተመላሾቹ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቆንስላ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄነራል ተወካይ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!