Fana: At a Speed of Life!

የተሻለ ውጤት ያስመዘገቡ የመንግስት ሆስፒታሎች የሽልማት መርሃግብር እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 28፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)የ2013 ሶስተኛው ዙር ሃገር አቀፍ የኢትዮጵያ ሆስፒታሎች ጥምረት ለጥራት ፕሮግራም የተሻለ ውጤት ላስመዘገቡ የመንግስት ሆስፒታሎች የሽልማት መርሃግብር እየተከናወነ ይገኛል።

ኢትዮጵያ ባለፉት አስርት አመታት የጤናውን ዘርፍ እንዲሻሻል በርካታ ስራዎች ሲከናወኑ መቆየቱን የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አንስተዋል።

በተለይም የጤና አገልግሎት አሰጣጡን ለተገልጋዩ እርካታን መፍጠር ላይ ትኩረቱን አድርጎ መስራት ተጠቃሽ እንደሆነም ሚንስትሯ ጠቁመዋል።

አሁን ላይ ደግሞ ምቹ እና ጽዱ የጤና ተቋማትን በመፍጠር ረገድ ላይ ትኩረት ተደርጎ ከክልል እና ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጋር እየተሰራ እንደሆነ ተነስቷል።

የዛሬው የእውቅናና ምስጋና ፕሮግራም በዚህ ረገድ የተሻለ አፈጻጸም ያሳዩትን የጤና ተቋማት ለማበረታታት እና የውድድር መንፈስ ፈጥሮ የሚፈለገውን ውጤት ለማምጣት ነው ተብሏል።

ሽልማቱ በክልል የተሻለ አፈጻጸም አሳይተው የተሸለሙትን እንደሚያካትት ነው የተገለጸው።

በጤና ዘርፉ የተሻለ ጥራት እና ምቹ የሆነ አገልግሎት መስጠትን ትኩረት ተደርጎ ሲሰራ መቆየቱም በመድረኩ ተገልጿል።

በዚህም የተሻለ የጤና ማዕከላትን ብቁ ከማድረግ እና ምቹ እንዲሆን ከማነሳሳት እንጻር እውቅና መስጠቱ ፈር ቀዳጅ እንደሚሆንም ተነስቷል።

በይስማው አደራው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.