Fana: At a Speed of Life!

15ኛው ዓለም አቀፍ የናይሎ ሳህራን ጉባኤ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 28፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) 15 ኛው ዓለም አቀፍ የናይሎ ሳህራን ጉባኤ እየተካሄደ ይገኛል።

15ኛው የናይሎ ሳህራን ቋንቋዎች ጉባኤ በበይነ መረብ በአራት የተለያዩ ማዕከላት እየተካሄደ ነው።

ጉባኤው በኢትዮጵያ፣ በኬኒያ፣ በደቡብ ሱዳን እና በሱዳን እየተካሄደ ሲሆን፥ ከተለያዩ የዓለም ሀገራት የተውጣጡ የመስኩ ሊቃውንት ተሳታፊዎች ናቸው።

በኢትዮጵያ በርካታ ቋንቋዎች የናይሎ ሳህራን (የአባይ ሳህራዊ ) አቢይ የቋንቋ ቤተሰብ አካል ሲሆኑ÷ ከኢትዮጵያ ውጭም የአባይ ወንዝን ተከትሎ በሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን፣ በኬኒያ እና በሌሎች የሰሜን እና ማዕከላዊ አፍሪካ ሀገራት ውስጥ በስፋት የሚነገሩ ቋንቋዎች ይገኙበታል።

በጉባኤው በአዲስ አበባ ማዕከል ከአዲስ አባበ ዩኒቨርሲቲ የቋንቋዎች እና ባህሎች አካዳሚ፣ ከባህል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር እና የኤስ አይ ኤል ኢትዮጵያ የቋንቋ ባለሙያዎች እና ወዳጆች ተገኝተዋል።

ጉባኤው በዋናነት በናይሎ ሳህራን (አባይ ሳህራዊ) ቋንቋዎች ስርዓተ ጽሕፈት፣ ሰዋስዋዊ መዋቅር፣ መዛግብተ ቃላት፣ ስለቁጥር ፣ ቅጥያዎች፣ ስለገላጮች እና መሰል ጉዳዮች ትኩረቱን አድርጎ እየተካሄደ መሆኑን የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.