Fana: At a Speed of Life!

የሃዋሳ ጉምሩክ ቅርንጫፍ 630 ሚሊየን ብር ለመንግስት ገቢ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 28፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በበጀት አመቱ በኮንትሮባንድ መቆጣጠር ስራ 630 ሚሊየን ብር ለመንግስት ገቢ ማድረጉን በጉምሩክ ኮሚሽን የሀዋሳ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ገለፀ።
የቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱ የህግ ተገዢነት ምክትል ስራ አስኪያጅ ኢዴሳ ለማ ለጣቢያችን በቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱ ካሉ ስምንት የመቆጣጠሪያ ኬላዎች የጪጩና ኮንሶ መቆጣጠሪያ ጣቢያዎች ለአፈፃፀሙ ትልቅ ድርሻ እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡
በ2014 የበጀት ዓመት 1 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ለመንግስት ገቢ ለማድረግ ማቀዱን የገለፀው ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቱ ከዚህ ውስጥ 1 ቢሊየን ብሩ ከኮንትሮባንድ መቆጣጠር ስራው የሚገኝ መሆኑን አቶ ኢዴሳ ለማ ገልጸዋል።
ኮሚሽኑ አሰራሩን ቀልጣፋ ለማድረግ ዘመናዊ መቆጣጠሪያ ካሜራዎችን ለመትከል ዝግጅት መጨረሱን ገልጿል።
በዚህም መጨናነቅና መዘግየት በከፍተኛ ሁኔታ የሚታይባቸው የሻሸመኔና ጪጩ መቆጣጠሪያ ኬላዎች ቅድሚያ ይሰጣቸዋል ተብሏል።
በመቅደስ አስፋው
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.