Fana: At a Speed of Life!

የአውስትራሊያ ተመራማሪዎች የኮሮና ቫይረስን ሊፈጥሩ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 20፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአውስትራሊያ ተመራማሪዎች የኮሮና ቫይረስን ከቻይና ውጭ ለመጀመሪያ ጊዜ ሊፈጥሩ መሆኑን አስታወቁ።

ተመራማሪዎቹ በሜልቦርን የቫይረሱን ቅጅ በቫይረሱ ከተጠቃ ሰው ናሙና በመውሰድ በድጋሚ ለመፍጠር እየሰሩ መሆኑን ገልጸዋል።

የሚፈጠረውን ቫይረስ ግኝትም የዓለም ጤና ድርጅት እንዲያውቀው ይደረጋል ተብሏል።

የተመራማሪዎቹ ጥረት የቫይረሱን ባህሪ በደንብ ለማወቅና ብሎም ለማከም የሚደረገውን ጥረት ያግዛል ተብሎ ታምኖበታል።

የቫይረሱ ተመሳሳይ ቅጅ በሚደረግ የሙከራ ሂደት እንደ መቆጣጠሪያ ሆኖ ያገለግላልም ነው የተባለው።

የቻይና ተመራማሪዎች የቫይረሱን ተመሳሳይ መፍጠራቸውን ገልጸው ነበር።

በኮሮና ቫይረስ እስካሁን 132 ሰዎች ለህልፈት ሲዳረጉ ወደ 6 ሺህ ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ መጠቃታቸው ታውቋል።

ቫይረሱ ከቻይና ውጭ በ16 ሃገራት ሲዛመት 47 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.