Fana: At a Speed of Life!

ከቤኒሻንጉል ክልል ከመከላከያ ሠራዊት ጎን ለመሠለፍ ፈቃደኛ ለሆኑ ወጣቶች ሽኝት ተደረገ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 28 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከመከላከያ ሠራዊት ጎን በመሠለፍ አሸባሪውን የሕወሓት ቡድን ለመፋለም ቁርጠኛ ለሆኑ ወጣቶች ሽኝት ተደረገላቸው።

ከክልሉ የተለያዩ ወረዳዎች የተውጣጡት እና ሠራዊቱን ለመቀላቀል ሙሉ ፈቃደኛ የሆኑት ወጣቶች በሃገር ሽማግሌዎች ምርቃትና ጸሎት የተሸኙ ሲሆን የኢትዮጵያን ሠንደቅ ዓላማ ተረክበዋል፡፡

የሃገር ሽማግሌዎቹ ወጣቶቹ ሃገር ላቀረበችው ጥሪ ምላሽ በመስጠት ጀግናውን የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በመቀላቀላቸው ዕድለኛ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

ሀገሪቱ ባላት ረዥም ታሪክ ተደፍራ አታውቅም፤ ወደፊትም በቁርጠኛ ልጆቿ አትደፈርም ያሉት የሃገር ሽማግሌዎቹ፥ ለሃገር ጥሪ ምላሽ ከመስጠት በላይ ጀግንነት የለምና ልትኮሩ ይገባል ብለዋል፡፡

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አብድልአዚም መሃመድ በበኩላቸው፥ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በሶስት ማዕከላት በርካታ ወጣቶች የመከላከያ ሠራዊትን ለመቀላቀል ሙሉ ፈቃደኛ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

ወጣቶቹ በበኩላቸው መከላከያ ሠራዊትን ለመቀላቀል የወሰኑት በራሳቸው ፈቃድ መሆኑን ገልጸው ከሠራዊቱ ጎን በመሰለፍ መስዋዕትነት ጭምር ለመክፈል ተዘጋጅተናል ማለታቸውን ከክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.