የሀገር ውስጥ ዜና

ለትግራይ እና ለሌሎች አከባቢ ተረጁዎች የሚሆን የእርዳታ እህል ክምችት በመጋዘን አለ-ሳማንታ ፓውር

By Tibebu Kebede

August 05, 2021

 

አዲስ አበባ ፣ሐምሌ 29፣ 2013 ( ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ያለው መጋዘን 58 ሺህ ሜትሪክ ቶን እህል ይዟል ነው ያሉት የአሜሪካው ዓለም አቀፍ ልማት ኤጀንሲ (ዩ ኤስ ኤድ) ኃላፊ ሳማንታ ፓወር ።

ሳማንታ ፓውር በቲውተር ገጻቸው እንዳሰፈሩት የእርዳታ እህሉ ተረጂዎች ጋር ለማድረስ ምቹ ሁኔታ ሊፈጠር ይገባል ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

አሸባሪው ሕወሃት እያደረገ ያለው ወታደራዊ እንቅስቃሴ እንዳሳሰባቸው ሳማንታ ፓወር ትናንት ከኢትዮጵያ ከፍተኛ የመንግስት ሀላፊዎች ጋር ሲወያዩ ማንሳታቸው ይታወሳል።

የአለም ምግብ ፕሮግራም ከዚህ በፊት አሸባሪው የህወሃት ቡድን የሰብዓዊ እርዳት ለተረጂዎች እንዳላደርስ እንቅፋት ፈጥሮብኛል ማለቱ አይዘነጋም።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!