Fana: At a Speed of Life!

አልማ ከራያ ዋግና ቆቦ ለተፈናቀሉ ወገኖች ከ300 ኩንታል በላይ የዱቄት ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 29 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ልማት ማህበር (አልማ) ከራያ ዋግና ቆቦ ለተፈናቀሉ ወገኖች ከ300 ኩንታል በላይ የዱቄት ድጋፍ አድርጓል።

የድርጅቱ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አራጋው ታደሰ ማህበሩ ከዘላቂ ልማት ባሻገር በተለያዩ ችግሮች ምክንያት ለሚፈናቀሉ ዜጎች ድጋፍ በማድረግ ሰፊ ስራ በመስራት ላይ እንደሚገኝ ገልጸው÷ ይሄ ድጋፍም የዚህ አካል መሆኑን አንስተዋል።

አልማ በደሴና በወልዲያ ለሚገኙ ተፈናቃዮች የሚከፋፈል 327 ኩንታል ዱቄት ለሰሜን ወሎ ዞን ለዋግኸምራ ብሄረሰብ ዞንና ለደቡብ ወሎ ዞን አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ጽህፈት ቤቶች አስረክቧል።

ለድጋፉም ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ ማህበሩ ወጪ ማድረጉንም ለማወቅ ተችሏል።

ወጪው ማህበሩ ካለው መደበኛ በጀት ላይ በማንሳት ለህዝቡ ወቅታዊ ችግር ለመድረስ ታስቦ የተከናወነ መሆኑም ተገልጿል።

በስንታየሁ መሀመድ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.