Fana: At a Speed of Life!

ፓትሪያርኩ ምዕመኑ ጾመ ፍልሰታን ለሀገር ሰላም በመጸለይ እንዲያሳልፍ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 29፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኞች ጾመ ፍልሰታን የተቸገሩትን በመርዳትና ለሃገር ሠላምና አንድነት በመፀለይ አንዲያሳልፉ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትሪያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘ-ኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት አሳሰቡ።

ብጹዕነታቸው በሀገር ውስጥና በመላው ዓለም ለሚገኙ አማኞች ለ2013 ጾመ ፍልሰታ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ለ16 ቀናት በሚዘልቀው ጾም ፀሎተ ምህላ እንዲደረግ በሲኖዶስ መወሰኑንም ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቀኖና ቤተ ክርስቲያን ድንጋጌ መሰረት ከሚጾሙ ሰባት አፅዋማት መካከል ጾመ ፍልሰታ ለማርያም አንዱ መሆኑን ፓትሪያርኩ አስታውሰዋል።

ፆመ ፍልሰታ የእምነቱ ተከታዮች አዛውንት፣ ሕጻናትና ወጣቶች በተመስጦና በመንፈሳዊ ስሜት በረከትና ረድኤት ለማግኘት የሚጾሙት መሆኑ የተለየ ያደርገዋል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ጾሙ የተቸገሩትን በመርዳት፣ የተራቡትን በማጉረስና የታረዙትን በማልበስ ሊሆን እንደሚገባም አሳስበዋል።

ሕዝበ ክርስቲያኑ ራሱን ከኮቪድ-19 በመጠበቅ ጾሙን ለኢትዮጵያ ሰላምና አንድነት በመፀለይ እንዲያሳልፍም ጥሪ አቅርበዋል።

ብፁዕነታቸው አማኞች ጾሙን ሲጾሙ በቀኖና ቤተክርስቲያን መሰረት የጾም መሳሪያዎች የሆኑትን ሠላም፣ ፍቅር፣ ጸሎት ምጽዋትና ትዕግስትን በመተግበር እንዲያሳልፉም መልዕክት አስተላልፈዋል።

ጾመ ፍልሰታ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች ከነሃሴ 1 ጀምሮ በጾምና በጸሎት ለ16 ቀናት ፈጣሪያቸውን በመለመን የሚያሳልፉት ነው።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.