Fana: At a Speed of Life!

በሀረሪ ክልል የዋጋ ንረት እንዲባባስ ባደረጉ የንግድ ተቋማት ላይ እርምጃ እየተወሰደ  ነው

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 29 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀረሪ ክልል ምርቶችን በመደበቅ የዋጋ ንረት እንዲባባስ ባደረጉ የንግድ ተቋማት ላይ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን የክልሉ የሀረሪ ክልል ንግድና ልማት ኤጀንሲ አስታወቀ።

የኤጀንሲ ኃላፊ አቶ ቡሽራ አሊዪ እንደገለፁት÷ እንደ ሀገር የተከሰተ የዋጋ ግሽበት ቢኖርም በክልሉ እየታየ የሚገኘው ህገወጥ የንግድ እንቅስቃሴ የበለጠ እንዲባባስ አድርጓል።

በክልሉ የምርት እጥረት ባይኖርም አንዳንድ አከፋፋዮችና ነጋዴዎች  ምርቶችን በመደበቅ የዋጋ ንረት እንዲባባስ እያደረጉ መሆኑን ጠቁመዋል።

በዚህም በክልሉ የገበያ ስፍራዎች በተደረገ ክትትልና ቁጥጥር በ38 አከፋፋዮች ላይ እርምጃ መወሰዱን መግለፃቸውን ከክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

እየተደረገ ባለው የክትትልና ቁጥጥር ስራም ህብረተሰቡ የነቃ ተሳትፎ እያደረገ ስለመሆኑ ያነሱት አቶ ቡሽራ በቀጣይም ከህዝቡና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት የዋጋ ንረት እንዲባባስ በሚያደርጉ ነጋዴዎች እና ተቋማት ላይ እየተወሰደ ያለው እርምጃ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.