የሀገር ውስጥ ዜና

ዳያስፖራው ኢትዮጵያን የሚጎበኙበት መርሃ ግብር ተዘጋጀ

By Melaku Gedif

August 05, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 29፣ 2013 በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ከመጪው ጳጉሜን 1 እስከ ጥቅምት 15 ቀን 2014 ዓም ሀገራቸውን የሚጎበኙበት መርሃ ግብር መዘጋጀቱን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ የተግባር ምክር ቤት አስታወቀ።

የጉብኝት መርሃ ግብሩ “እንቁጣጣሽ ኢትዮጵያ የፍቅር ጉዞ ዓባይን እንጎብኘው” በሚል መሪ ሃሳብ ነው የሚካሄደው። በመርሃ ግብሩ ዳያስፖራው የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታን እንደሚጎበኝና የግድቡን ሠራተኞች እንደሚያበረታታ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ የተግባር ምክር ቤት የሕዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ አለባቸው ደሳለኝ ገልጸዋል።