Fana: At a Speed of Life!

አሸባሪው ትህነግ ከ“አልቃይዳ እና አይኤስ” የበለጠ የሽብር ድርጊት መፈጸሙ ተገለጸ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 30 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የሽብር ድርጊት በመፈጸም አሸባሪው ትህነግ ከአልቃይዳ እና አይኤስ የበለጠ አሰቃቂ እና አስነዋሪ ድርጊቶችን የፈጸመ መሆኑን የአማራ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ግዛቸው ሙሉነህ ገለጹ፡፡
በኢትዮጵያ ያልተፈጸመ በደል የለም የሚሉት ዳይሬክተሩ ከኢቲቪ ጋር በነበራቸው ቆይታ “ማንነታችንን የሰረቀ፣ ታሪካችንን ያበላሸ፣ ብሔርን ከብሄር፣ ሃይማኖትን ከሃይማኖት ሲያጋጭ የኖረ፣ በአጠቃላይ ሃይማኖታዊ ትውፊቶችን ሳይቀር እንዲሸረሸሩ ያደረገና ማህበረሰባዊ ስነ ምግባር ጭምር እንዲዛባ ይሰራ የነበረ ቡድን ነው” ብለዋል፡፡
ይህ አሸባሪ ድርጅት በአረመኔያዊ ድርጊቱ በርካቶችን በጅምላ እየገደለ ሲቀብር የኖረ፣ በፖለቲካ አሻጥር የሚታወቅ፣ የዓለም አቀፉን ማህበረሰብ የሚያዛባ እና አገር እንዲበጠበጥ፣ እንዲፈርስና እንዲበተን ከውጭ ጠላቶች ጋር ጭምር እየሰራ ያለ ድርጅት መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በአሁኑ ጊዜ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ አሸባሪው ህወሓት ቀድሞ በሰራው የሴራ ፖለቲካ ምክንያት እውነትን ሊሰሙ ፈቃደኛ አለመሆናቸው እየታየ መሆኑን ነው አቶ ግዛቸው የገለጹት፡፡
“እውነት ያለው እኛ ጋር ሆኖ ሳለ ውሸት እውነት ሆኖ እየተነገረ ነው” የሚሉት ዳይሬክተሩ፣ አስፈላጊ ባልሆነ መንገድ የሱዳን ኮሪደር ይከፈት እያሉ ያሉትም የዚህ የፖለቲካ አሻጥር ውጤት ነው” ማለታቸውን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡
አሸባሪው ትህነግ መንግስት የተናጠል ተኩስ አቁም አውጆ እያለ በአማራ ክልል በፈፀመው ትንኮሳ ከ200 ሺህ የሚለቅ የክልሉ ነዋሪዎችን ከቀያቸው አፈናቅሎ እርዳታ ጠባቂ ማድረጉን በመግለፅ ይህ አሸባሪ ቡድን እስኪጠፋ መታገል የሁሉንም ትብብር የሚጠይቅ ነው ብለዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.