Fana: At a Speed of Life!

የወልድያ ሰላም ተጠብቆ እንዲዘልቅ የከተማዋ ወጣቶች እያደረጉት ያለውን ተጋድሎ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ተጠየቀ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 30 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የወልድያ ሰላም ተጠብቆ እንዲዘልቅ የከተማዋ ወጣቶች እያደረጉት ያለውን ተጋድሎ አጠናክረው እንዲቀጥሉ የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ሙሐመድ ያሲን ጠየቁ።
 
የወልድያ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ሙሐመድ ያሲን እንዳሉት÷ወልዲያ ተስፋፊውና ሰው በላው አሸባሪው የትህነግ ቡድን በእጅጉ ከሚመኛት ከተማ አንደኛዋ ናት።
 
በወልድያና አካባቢው የሚገኙ ወጣቶች ከመቼውም ጊዜ በላይ ራሳቸውን አደራጅተው እና አንቅተው ከከተማ አስተዳደሩ፣ ከዞኑ አስተዳደርና ከጸጥታ ተቋሙ ጋር በቅንጅት አካባቢን የመጠበቅ ሥራ እየሠሩ ነው ብለዋል።
 
የከተማዋ ቁልፍ የሚባሉ በሮችና ለጥቃት ያጋልጣሉ የሚባሉ ተራራዎችን በንቃት የመጠበቅ ሥራ እየተሠራ መሆኑንም ገልጸዋል።
 
ወደ ከተማዋ የሚቃጡ የትኛውንም አደጋ በመከላከል እና ተላለኪዎችን በመቆጣጠር ላይ መሆናቸውንም ጠቁመዋል።
 
ከተማዋ እንደወትሮው ሁሉ ሰላማዊ እንቅስቃሴ ላይ ናት ያሉት ከንቲባው÷የጠላት ሃይል ወልድያን እንደተቆጣጠረ አድርጎ የሚያናፍሰው ወሬ ውሸት ነው፤ ከከተማዋ ነዋሪዎች የበለጠ አስረጅ የለም ነው ያሉት።
 
የከተማዋ ወጣቶችና ነዋሪዎች ጠላት የሚገባበትን ቀዳዳ በመድፈን እያሳዩት ያለውን ጥንካሬ አጠናክረው እንዲቀጥሉም መጠየቃቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡
 
የከተማዋ ነዋሪዎች ሳይደናገጡ የየዕለት ሕይወታቸውን እንዲቀጥሉም አስገንዝበዋል።
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.