Fana: At a Speed of Life!

በመተከል ዞን የመከላከያ ሰራዊትን ለሚቀላቀሉ ወጣቶች ሽኝት ተደረገ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 30 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ከመተከል ዞን ሁሉም ወረዳዎች የመከላከያ ሰራዊትን ለመቀላቀል ለወሰኑ ወጣቶች ሽኝት ተደረገ፡፡
በሽኝት መርሃ ግብሩ ላይ የሀገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች የተገኙ ሲሆን ወጣቶቹ በህልውናው ዘመቻ ከሰራዊታችን ጎን ለመሰለፍ መወሰናቸው፣ የወጣቱ አገራዊ ሰሜት እያደገ መምጣቱን ያመላክታል ብለዋል። ለወጣቶቹ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ በክብር አስረክበው ሸኝተዋቸዋል።
በመርሃ ግብሩ ላይ የ7ኛ ሜካናይዝድ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ ኮሎኔል በስፋት ፈንቴ እና የቤኒሻንጉል ክልል መንገድ ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ቀልቤሳ ዋቅጅራ ንግግር አድርገዋል፡፡
ኮሎኔል በስፋት ፈንቴ በንግግራቸው በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል የሚካሄደው ፍልሚያ ኢትዮጵያን በስሟ ለመጥራት እንኳ ተፀይፈው ሀገር ለማፍረስ በተነሱና ኢትዮጵያን ከመፍረስ ለመታደግ በሚፋለሙ ሀይሎች መካከል እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.