Fana: At a Speed of Life!

56 ኩንታል ሃሺሽ በሁመራ ከተማ በቁጥጥር ስር ዋለ

 

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሁመራ ከተማ ባለፉት ሁለት ቀናት 56 ኩንታል ሃሺሽ ሲዘዋወር በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡

የሃሺሹን መነሻ ለማወቅ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር አውሎ እያጣራ መሆኑንም ፖሊስ አስታውቋል፡፡

አሸባሪው የህወሓት ቡድን ከሰሞኑ በአማራ እና በአፋር ክልሎች በከፈተው ወረራ በግዳጅ ወደ ጦርነት የሚማግዳቸውን ህጻናት እና ወታደሮች አደንዛዥ እጾችን እየተጠቀመ ወደ ጦርነት እንደሚያሰማራ ሲገለጽ መቆየቱ ይታዎሳል፡፡

ባለፉት ሁለት ቀናት ብቻ በሁመራ ከተማ ከተያዘው 56 ኩንታል ሃሺሽ ውስጥ ትናንት ማምሻውን የተያዘው 48 ኩንታል ሃሺሽ በማኅበረሰቡ ጥቆማ እና ክትትል የተያዘ ነው ፡፡

ሃሺሹን የጫነው ተሽከርካሪ ከሃሺሹ በላይ ሸንኮራ አገዳ ጭኖ ለማሳለፍ ሲሞክር በህዝብና በጸጥታ ኃይሎች ትብብር በቁጥጥር ስር ውሏል።

የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ፖሊስ መምሪያ የወንጀል መከላከል ዋና ክፍል ኃላፊ ኮማንደር አትንኩት አያሌው ሐምሌ 27 እና 29/2013 ዓ.ም በከተማዋ 56 ኩንታል ሃሺሽ በቁጥጥር ስር ውሏል ብለዋል፡፡

ከሰሞኑ አሸባሪው የትህነግ ቡድን ወረራ በፈጸመባቸው አካባቢዎች ላይ ላሰማራቸው ወታደሮች አደንዛዥ እጾችን ይጠቀም እንደነበር ተግልጿል ያሉት ኮማንደር አትንኩት፣ ምናልባትም በቁጥጥር ስር የዋለው ሃሺሽ ለዚህ አገልግሎት ለማዋል የታሰበ ሊሆን ይችላል ብለዋል፡፡

በሁመራ ከተማ ሕዝቡ እየሰጠው ያለውን ጥቆማ ያደነቁት ኮማንደርሩ ፣ ትብብሩ በቀጣይም ተጠናክሮ እንዲቀጥል እና ኬላዎች ላይ የተጠናከረ ፍተሻ እንዲኖር፣ መሃል ሀገርም ተመሳሳይ ቁጥጥሮች እንዲጠናከሩ አሳስበዋል፡፡

ማይካድራን ጨምሮ በዞኑ በርካታ አካባቢዎች አሸባሪው ቡድን አደንዛዥ እጾችን ቀደም ሲል በስፋት ያንቀሳቅስ እንደነበርም የመምሪያ ኃላፊው ተናግረዋል፡፡

ምንጭ:- አሚኮ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.