Fana: At a Speed of Life!

የፕላንና ልማት ኮሚሽን እና የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን በዲጂታል ክትትልና ሪፖርት አቀራረብ ሥርዓት ዙሪያ የልምድ ልውውጥ አደረጉ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ፕላንና ልማት ኮሚሽን ከአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን ጋር በዲጂታል የክትትልና ሪፖርት አቀራርብ ሥርዓት ዙሪያ የልምድ ልውውጥ አድርገዋል።

የልምድ ልውውጡ ጠቃሚ አሰራር ዘዴዎችን ከአንዱ ወደሌላው ለማስተላፍ እንዲሁም የሚኖሩ ጉድለቶችን እና ክፍተቶችን ለመሙላት የታሰበ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

በዌብናር በመታገዝ በተካሄደው በዚህ የልምድ ልውውጥ ዶክተር ታደለ ፈረደ በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን የተዘጋጀውን” IPRT” የተሰኘው ሥርዓት አቅርበዋል፡፡

በፕላንና ልማት ኮሚሽን የተዘጋጀው የዲጂታል ክትትልና ሪፖርት አቀራረብ ሥርዓት(D~MRS) በበፕላንና ልማት ኮሚሽን አማካሪ በሆኑት አቶ ሰለሞን ተስፋሥላሴ በኩል ቀርቧል።

በሁለቱ የዲጂታል ክትትልና ሪፖርት አቀራርብ ሥርዓቶች ዙሪያ ውይይቶች ተደርጎ ከሁለቱም በኩል ማብራሪያዎች ተሰጥተዋል፡፡

የልምድ ልውውጡ ከአንደኛው ወገን ያለውን ክፍተት ከሌላው በመማር ክፍተቱን የማሟላት ዕድል እንዲፈጠር ከማድረጉም በላይ በክትትልና ግምገማ ሥርዓት ዙሪያ በተለይም የተቀናጀ ዲጂታል የዕቅድ ክትትልና ግምገማ አሰራሮችን ለማጎልበት ፋይዳው ከፍተኛ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

ሁለቱ ተቋማት ከዚሁ ጋር በተገናኘ በቀጣይ ትኩረት አድርገው በጋራ መስራት ያለባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡

በአንዋር አብራር

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.