Fana: At a Speed of Life!

ኮሚሽኑ በ2013 ዓ.ም እቅድ አፈጻጸሙና በ2014 በጀት ዓመት ዕቅዱ ዙሪያ እየተወያየ ነው

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴራል ጉምሩክ ኮሚሽን የ2013 በጀት አመት ዕቅድ አፈጻጸም ና የ2014 በጀት አመት ዕቅድ ምክክሩን በሀዋሳ ከተማ እያካሄደ ነው።

በመድረኩ ላይ የኮሚሽኑ ኮሚሽነር አቶ ደበላ ቃበታ ፣ ምክትል ኮሚሽነሮች፣ ዳይሬክተሮች፣ የቅርንጫፍ መስሪያ ቤቶች ስራ አስኪያጆችና ምክትል ስራ አስኪያጆች ተገኝተዋል።

ኮሚሽኑ በ2013 የበጀት ዓመት 125 ቢሊየን ብር አቅዶ 112 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር ማሳካት መቻሉ ተገልጿል፡፡

ይህም የዕቅዱ 89 ከመቶ መሆኑ ነው የተመላከተው፡፡

በመቅደስ አስፋው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.