Fana: At a Speed of Life!

የካፋ ባህል ማዕከል በአዲስ አበባ ሊገነባ ነው

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የካፋ ባህል ማዕከል ግንባታ የሚሆን የቦታ ርክክብ ሥነ-ሥርዓት በአዲስ አበባ ተካሄደ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ለከፋ ህዝቦች ባህል ማዕከል መገንቢያ ቦታ አስረክበዋል።

በርክክብ መርሐግብሩ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ፣የከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ሚኒስትሯ ኢ/ር አይሻ መሀመድ ፣ የደቡብ ክልል አፈጉባኤ ወ/ሮ ሄለን ደበበ ፣ለካፋ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ በላይ ተሰማ እና የፌደራል እና የከተማ አአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም እና የዞን ተወላጆች ተገኝተዋል ።

ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በካርታ ርከክቡ እንደገለፁት፣ የካፋ ባህል ማዕከል አዲስ አበባ ላይ ለመገንባት እቅድ ሲያዝ የኢትዮጵያን ብሄር ብሄረሰቦች እርስ በእርስ ከማቀራረባቸው ባለፈ ለከተማዋ የቱሪስት መዳረሻ መሆን እንዲያስችሉ ታሳቢ በማድረግ ነው ብለዋል።

ህዝባችን ባለው ልዩ ልዩ የባህል እና የማንነት እሴት በጋራ በአንድነት ቆመው ኢትዮጵያን ማጽናት እና መጠበቅ ይገባል ያሉት ምክትል ከንቲባዋ አሁንም በኢትዮጵያ ላይ የተጋረጠውን የመበታተን አደጋ ሁሉም በጋራ መቆም እንደሚገባ ተናግረዋል ።

የከፋ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ በላይ ተሰማ በበኩላቸው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሰጣቸው 5ሺህ ካሬሜትር ቦታ ላይ የዞኑ ህዝብ ባህሉን እና እሴቱን ለማስተዋወቅ ከፍተኛ እድል ይፈጥራል ማለታቸውን ከከተማ አስተዳደሩ ፕሬስ ስክሬተሪያት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ከተማ አስተዳደሩ ላደረገው የመሬት ስጦታ በከፋ ዞን ህዝብ ስም ያመሰገኑት ምክትል አስተዳደሪው የባህል ማዕከሉን በአጭር ጊዜ ውስጥ ለመገንባት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል ።

የከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ሚኒስትሯ ኢ/ር አይሻ መሀመድ በዚሁ ጊዜ እንዳስታወቁት በከተማዋ በተለያዩ ጊዜያት ቦታ ለተሰጣቸው ለኢትዮጵያን ብሄር ብሄረሰቦች ባህል ማዕከላት ግንባታ ከዲዛይን ስራ ጀምሮ አስፈላጊውን ሙያዊ ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል።

ተጨማሪ መረጃ፡- ኢዜአ

 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.