Fana: At a Speed of Life!

የወላይታ ሶዶ ግብርና  ኮሌጅ  ያሰለጠናቸውን 3ሺህ 226  ተማሪዎችን አስመረቀ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የወላይታ   ሶዶ ግብርና ኮሌጅ  ለ18ኛ ዙር በደረጃ 4 ያሰለጠናቸውን 3ሺህ 226  ተማሪዎችን አስመረቀ ።

የኮሌጁ  ዲን  ረዳት ፕሮፈሰር መርክነ  መሰኔ  በአራት  የስልጠና መስኮች ለሦስት ተከታታይ ዓመታት በንድፈ ሃሳብና በተግባር የሰለጠኑ ተማሪዎች በዛሬው እለት መመረቃቸውን ተናግረዋል፡፡

ግብርና  ለሀገር እድገት የጀርባ አጥንት በመሆኑ  ሰልጣኞች ባገኙት በቂ እውቀት ሀገራቸውን እንዲያገለግሉ ጥሪ አቅርበዋል።

ኮሌጁ  ከቴክኒክና  ሙያ ደረጃ  በመውጣት ወደ ሙሉ ኮሌጅ በተሸጋገረበት ጊዜ ተማሪዎች መመረቃቸው ታሪካዊ ያደርጋችዋል ነው ያሉት፡፡

የኮሌጁ አስተዳደር ቦርድ ሰብስቦ እና የእለቱ የክብር እንግዳ አቶ  ዳንኤል ዳምጠው ግብርና የስራ እድል ከመፍጠሩ በተጨማሪ ከ80 በመቶ  በላይ ለሀገራችን ህዝብ  መተዳደሪያ ነው ብለዋል ።

መራቂ  ሰልጣኞች ከሥራ ጠባቂነት እና ከኃላ ቀር አስተሳሰብ በመላቀቅ ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍሎሽን በቅንነት በማገልገል ለሀገራችን  እድገት የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ጥሪ አስተላልፈዋል ።

ተመራቂ ሰልጣኞችም በሰለጠኑበት ሙያ የአርሶ እና አርብቶ አደሩን ኑሮ ለመለወጥ  እንደሚሰሩ ተናግረዋል ።

ኮሌጅ  ላለፉት 19 ተከታታይ ዓመታት የዛሬን ተመራቂዎችን ጨምሮ ከ22 ሺህ በላይ ስልጣኞችን በማስመርቅ ለግብርና ስራ የበኩሉን ድርሻ አበርክቷል ።

 

በማቴዎስ ፈለቀ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.