ስፓርት

አትሌት ለተሰንበት ግደይ ለኢትዮጵያ ተጨማሪ ሜዳልያ አስገኘች

By Tibebu Kebede

August 07, 2021

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በቶኪዮ ኦሊምፒክ 10 ሺህ ሜትር የሴቶች የሩጫ ውድድር አትሌት ለተሰንበት ግደይ ለኢትዮጵያ ተጨማሪ ሜዳልያ አስገኝታለች።

አትሌት ለተሰንበት ውድድሩን 3ኛ በመሆን አጠናቃለች።

በውድድሩ ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ሲፋን ሃሰን 1ኛ ስትሆን ሌላኛዋ ትውልደ ኢትዮጵያዊት ቃል ኪዳን ገዛኸኝ 2ኛ በመሆን ውድሯን አጠናቃለች።