Fana: At a Speed of Life!

ከ2 ቢሊየን ብር በላይ በሃሰተኛ ሰነድ ከባንክ ሊያወጡ የሞከሩ ሶስት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ2 ቢሊየን ብር በላይ በሃሰተኛ ሰነድ ከባንክ ሊያወጡ ሲሞክሩ የነበሩ ሶስት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

በፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ምርመራ ቢሮ የፋይናንስና ንግድ ወንጀሎች ምርመራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ረዳት ኮሚሽነር ብርሃኑ አበበ በሃሰተኛ ሰነድ ሊመዘበር የነበረው ገንዘብ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተቀመጠ የሳሊኒ ኮንስትራክሽን ሂሳብ መሆኑን ለኢቲቪ ገልፀዋል።

በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ስራ ላይ ተሰማርቶ ውጤታማ የሆነው የዚህ ኩባንያ ሂሳብ በሃሰተኛ ሲፒኦ ሊያጭበረብሩ ጉዞ ላይ እያሉ በቁጥጥር ስር የዋሉት ሶስቱ ተጠርጣሪዎች ተስፋሚካኤል ታመነ ፣ተክለብርሃን በርሄ እና መክብብ በላይ የተሰኙ ግለሰቦች ናቸው።

ተጠርጣሪዎቸ ዛሬ እኩለ ቀን አካባቢ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የተባበሩት ማደያ አካባቢ ለዚሁ ተግባር ከሚጠቀሙባቸው ተሽከርካሪዎች ጋር በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም ነው ረዳት ኮሚሽነር ብርሃኑ የተናገሩት።

ተጠርጣሪዎቹ ከአሸባሪው የህወሓት ቡድን ጋር ግንኙነት ሳይኖራቸው እንደማይቀርም ረዳት ኮሚሽነሩ ተናግረዋል።

በአሁኑ ሰአት የተጠርጣሪዎች መኖሪያ ቤት ከፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ከአራዳ ምድብ ችሎት በተገኘ የብርበራ ትዕዛዝ እየተፈተሸ መሆኑንም አብራርተዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.