ስፓርት

ብራዚል በቶኪዮ ኦሊምፒክ የወንዶች እግር ኳስ አሸናፊ ሆነች

By Tibebu Kebede

August 07, 2021

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ብራዚል በቶኪዮ ኦሊምፒክ የወንዶች እግር ኳስ አሸናፊ ሆነች።

በፍጻሜው ከስፔን ጋር የተገናኘችው ብራዚል ጨዋታውን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፋለች።

መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ አንድ አቻ የተጠናቀቀ ሲሆን፥ በተጨማሪ 30 ደቂቃዎች ብራዚል ተጨማሪ ጎል አስቆጥራ የውድድሩ አሸናፊ ሆናለች።

ለብራዚል የድል ጎሎቹን ሳንቶስ እና ማልኮም እንዲሁም ኦያርዛባል ደግሞ የስፔንን ብቸኛ ጎል አስቆጥሯል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!