የሀገር ውስጥ ዜና

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ አትሌት ለተሰንበት ባስመዘገበችው ውጤት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ

By Tibebu Kebede

August 07, 2021

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ አትሌት ለተሰንበት ግደይ በቶኪዮ ኦሊምፒክ 10 ሺህ ሜትር የሩጫ ውድድር ባስመዘገበችው ውጤት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ።

ፕሬዚዳንቷ “የዓለም ክብረወሰን ባለቤት አትሌት ለተሰንበት ግደይ የነሀስ ሜዳልያ በማግኘቷ እንኳን ደስ አለን” ብለዋል።

በወንዶች ማራቶን ውድድርም ለኢትዮጵያውያን አትሌቶች መልካም እድል መመኘታቸውን የፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!